ዮሐንስ 6:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስን በባሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታንኳዉ በቀረበ ጊዜም ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሀያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ። |
ወይኑም ከከተማው ውጭ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ተረገጠ፤ ከፍታው እስከ ፈረስ ልጓም የሚደርስ፣ ርዝመቱ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ደም ከመጭመቂያው ወጣ።
ከተማዪቱም ርዝመቷና ስፋቷ እኩል ሆኖ አራት ማእዘን ነበረች። እርሱም ከተማዪቱን በዘንጉ ለካ፤ ርዝመቷም ዐሥራ ሁለት ሺሕ ምዕራፍ ሆነ፤ ስፋቷና ከፍታዋም እንዲሁ ሆነ።