ዮሐንስ 6:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ ከተበላው ዐምስት የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቍርስራሽ ሰብስበው ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰለዚህም አከማቹ፤ ከበሉትም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ሰዎቹ በልተው ከተረፈው ከአምስቱ የገብስ እንጀራ ፍርፋሪውን ሰብስበው በዐሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሰበሰቡ፥ በልተው ከጠገቡ በኋላም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈው ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰለዚህ አከማቹ፥ ከበሉትም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሞላ። |
አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው፣ “ታዲያ ለእነዚህ ለእስራኤል ወታደሮች የከፈልሁት መቶ መክሊት እንዴት ይሁን?” ሲል ጠየቀው። የእግዚአብሔርም ሰው፣ “እግዚአብሔር ከዚህ አብልጦ ሊሰጥህ ይችላል” ሲል መለሰለት።