አንተ ለጽዮን የምሥራችን የምትነግር፤ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጣ፤ አንተ ለኢየሩሳሌም ብሥራት የምትነግር፣ ድምፅህን በኀይል ከፍ አድርገህ ጩኽ። ከፍ አድርገው፤ አትፍራ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ “እነሆ፤ አምላካችሁ!” በል።
ዮሐንስ 19:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶ ሐምራዊ ልብስም ለብሶ ወጣ፤ ጲላጦስም፣ “እነሆ፤ ሰውየው!” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ ቀይ ልብስም ለብሶ፥ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም “እነሆ ሰውዬው፤” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶና ቀይ ልብስ ለብሶ ወደ ውጪ ወጣ፤ ጲላጦስም “እነሆ፥ ሰውየው!” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላጦስም፥ “እነሆ፥ ሰውዬው” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። |
አንተ ለጽዮን የምሥራችን የምትነግር፤ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጣ፤ አንተ ለኢየሩሳሌም ብሥራት የምትነግር፣ ድምፅህን በኀይል ከፍ አድርገህ ጩኽ። ከፍ አድርገው፤ አትፍራ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ “እነሆ፤ አምላካችሁ!” በል።
አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤
“እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን?
እሾኽ ጐንጕነው አክሊል በመሥራት ራሱ ላይ ደፉበት፤ የሸንበቆ በትር በቀኝ እጁ በማስያዝ በፊቱ ተንበርክከው፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” በማለት አሾፉበት፤
የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።