ዮሐንስ 17:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ፣ እነርሱም ከዓለም ባለመሆናቸው ዓለም ጠልቷቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳልሆንሁ ሁሉ እነርሱም ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉም፤ ስለዚህ ዓለም ጠላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ቃልህን ሰጠኋቸው፤ ዓለም ግን ጠላቸው፤ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ እነርሱ ከዓለም አይደሉምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው። |
የክፉው ወገን ሆኖ ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየን አትሁኑ፤ ለምን ገደለው? ምክንያቱም የርሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።