ከዚያም ሴቲቱ ኤልያስን፣ “አሁን የእግዚአብሔር ሰው መሆንህን፣ ከአንደበትህም የወጣው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ዐወቅሁ” አለችው።
ዮሐንስ 16:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ሁሉን ነገር እንደምታውቅና ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ ተረድተናል፤ ይህም ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እንድናምን አድርጎናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ፥ እንዲሁም ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማያስፈልግህ አሁን ዐወቅን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ወጣህ እናምናለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን አንተ ሁሉን እንደምታውቅ፥ ማንም ሊነግርህ እንደማትሻ ዐወቅን፤ በዚህም ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን” አሉት። |
ከዚያም ሴቲቱ ኤልያስን፣ “አሁን የእግዚአብሔር ሰው መሆንህን፣ ከአንደበትህም የወጣው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ዐወቅሁ” አለችው።
ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ፣ “ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ እንዲሁም፣ ‘ወደ አብ ስለምሄድ’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ተባባሉ፤
ሦስተኛም ጊዜ፣ “የዮና ልጅ፣ ስምዖን ሆይ፤ ትወድደኛለህን?” አለው። ጴጥሮስም ሦስተኛ ጊዜ ኢየሱስ፣ “ትወድደኛለህን?” ብሎ ስለ ጠየቀው ዐዝኖ፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “በጎቼን መግብ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እርሱ ላከኝ እንጂ በገዛ ራሴ አልመጣሁም።
ከእግዚአብሔር ዐይን የተሰወረ ምንም ፍጥረት የለም፤ ስለ ራሳችን መልስ መስጠት በሚገባን በርሱ ፊት ሁሉም ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው።