ዮሐንስ 13:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እነዚህን ነገሮች ዐውቃችሁ ብትፈጽሙ ትባረካላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንን ስታውቁና ስታደርጉ ብፁዓን ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ዐውቃችሁ ብትሠሩ ብፁዓን ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባዮች ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘የዚህን ኪዳን ቃል ስሙ፤ አድርጉትም።