ዮሐንስ 1:48 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናትናኤልም “እንዴት ዐወቅኸኝ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ፣ ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ አየሁህ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናትናኤልም “እንዴት አወቅኸኝ?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ ዛፍ ሥር ሆነህ፥ አየሁህ፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናትናኤልም “የት ታውቀኛለህ?” አለው። ኢየሱስም “ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት ከበለስ ዛፍ ሥር ሆነህ አይቼሃለሁ” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይህ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ። |
አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።
እነርሱም በገሊላ ከምትገኘው ከቤተ ሳይዳ ወደ ሆነው ሰው፣ ወደ ፊልጶስ መጥተው፣ “ጌታ ሆይ፤ እባክህን ኢየሱስን ለማየት እንፈልጋለን” አሉት።
በልቡም የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ እንዲሁም፣ “እግዚአብሔር በርግጥ በመካከላችሁ ነው” በማለት በግንባሩ ተደፍቶ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።