ዮሐንስ 1:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ በዚያም ዕለት ዐብረውት ዋሉ፤ ከቀኑም ዐሥር ሰዓት ያህል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “መጥታችሁ እዩ፤” አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፤ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ ጊዜው ወደ ዐሥር ሰዓት ገደማ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄዱና የት እንደሚኖር አዩ። በዚያን ቀን ከእርሱ ጋር አብረው ዋሉ፤ ጊዜው ወደ ዐሥር ሰዓት ገደማ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ረቢ፥ ትርጓሜውም መምህር ሆይ፥ ማለት ነው፤ ወዴት ትኖራለህ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ ትርጓሜው መምህር ሆይ ማለት ነው። |
እነርሱ ግን፣ “ምሽት እየተቃረበ፣ ቀኑም እየተገባደደ ስለ ሆነ ከእኛ ጋራ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ ስለዚህ ከእነርሱ ጋራ ለማደር ገባ።
ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ “ረቢ” ማለት መምህር ማለት ነው።