ኤርምያስ 6:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂዎችን አቆምሁላችሁ፤ ‘የመለከትንም ድምፅ ስሙ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘አንሰማም’ አላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ ‘የመለከቱን ድምፅ አድምጡ’ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አናደምጥም’ አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን በኋላ እግዚአብሔር የማስጠንቀቂያውን ጥሩምባ ድምፅ የሚያሰሙ ጠባቂዎችን አቆመ፤ እነርሱ ግን “አንሰማም” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፥ “የመለከቱን ድምፅ አድምጡ” ብዬ ጠባቂዎችን ሾምሁባቸው፤ እነርሱ ግን፥ “አናዳምጥም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ የመለከቱን ድምፅ አድምጡ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፥ እነርሱ ግን፦ አናደምጥም አሉ። |
የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ድምፅ የለሽ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ተጋድመው ያልማሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም። እናንተ ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ ሕዝብ አምላኩን እግዚአብሔርን ያልታዘዘ፣ ምክሩን ያልተቀበለ ወገን ነው፤ እውነት ጠፍቷል፤ ከአንደበታቸውም ሸሽቷል።
ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።
የቀደሙት ነቢያት፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ይላል በማለት ለአባቶቻችሁ ሰብከው ነበር፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤” ይላል እግዚአብሔር።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም።