ኤርምያስ 52:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ሰዎቹን በሐማት ምድር በነበረችው በሪብላ ውስጥ አስገደላቸው። ይሁዳም ከምድሩ በዚህ ሁኔታ ተማርኮ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎንም ንጉሥ መታቸው፥ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም በዚያው አስደብድቦ በማሠቃየት በሞት ቀጣቸው። በዚህም ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ ከአገራቸው ተማርከው ተወሰዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎንም ንጉሥ መታቸው፤ በኤማትም ምድር ባለችው በዴብላታ ገደላቸው፤ እንዲሁ ይሁዳ ከሀገሩ ተማረከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎንም ንጉሥ መታቸው፥ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ። |
እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በዚያው ቀጠሉበት፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ከሀገሩ ተማርኮ ወደ አሦር ተወሰደ፤ አሁንም በዚያው ይገኛል።
ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “እስራኤልን እንዳስወገድሁ ሁሉ ይሁዳንም ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኋትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ብዬ የተናገርሁለትን ይህን ቤተ መቅደስ እተዋለሁ” አለ።
የተመሸገባት ከተማ ባዶዋን ቀርታለች፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወች ስፍራ ሆናለች፤ ጥጆች በዚያ ይሰማራሉ፤ እዚያም ይተኛሉ፤ ቅርንጫፎቿንም ልጠው ይበላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘አንተንና ወዳጆችህ ሁሉ ለሽብር እዳርጋለሁ፤ የገዛ ዐይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ። ይሁዳን ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
ከዚያ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ከመቅሠፍት፣ በከተማው ከሰይፍና ከራብ የተረፈውንም ሕዝብ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ሕይወታቸውን ለማጥፋት ለሚሹ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውምም።’
ንብረት ያልነበራቸውን ድኾች ግን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በይሁዳ ምድር ተዋቸው፤ በዚያ ጊዜም የወይን አትክልት ቦታና የዕርሻ መሬት ሰጣቸው።
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፤ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ። እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።
እግዚአብሔር አንተንና በላይህ ያነገሥኸውን ንጉሥ፣ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል፤ ከዚያም ከዕንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።
ከዚያም እግዚአብሔር ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትንሃል። በዚያ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከዕንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።
ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክሮች አድርጌ እጠራለሁ፤ በዚያ ቦታ ብዙ ዘመን አትኖሩም፤ ፈጽሞ ትጠፋላችሁ።