ኤርምያስ 52:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ከንጹሕ ወርቅና ብር የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ጐድጓዳ ሳሕኖችን ጥናዎችን፣ ወጭቶችን፣ ምንቸቶችን፣ መቅረዞችን፣ ጭልፋዎችንና ለመጠጥ ቍርባን ማቅረቢያ የሚሆኑ ወጭቶችን ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ወጭቶቹንና ማንደጃዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹንና የሸክላ ድስቶቹን፥ መቅረዞችንና ሙዳዮችን መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክብር ዘቡ አዛዥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ የዕጣን ማጠኛዎችን፥ ጐድጓዳ ወጭቶችን፥ ድስቶችን፥ መቅረዞችን፥ ጭልፋዎችን፥ የመጠጥ መሥዋዕት ማቅረቢያዎችን፥ በወርቅና በብር የተሠሩ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዦችም አለቃ ጽዋዎቹን፥ ማንደጃዎቹን፥ ድስቶቹንና ምንቸቶቹን፥ መቅረዞቹንና ጭልፋዎቹን፥ መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ጽዋዎቹንና ማንደጃዎቹን ድስቶቹንና ምንቸቶችን መቅረዞችንና ጭልፋዎቹን መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ። |
እርሱም፣ “ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ በዐናቱ ላይ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ፤ በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።
ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ ወጥቶ መቅሠፍት ጀምሯልና ጥናውን ወስደህ ዕጣን በመጨመር ከመሠዊያው እሳት አድርግበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበሩ ሄደህ አስተስርይላቸው” አለው።