ኤርምያስ 51:55 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ባቢሎንን ያጠፋታል፤ ታላቅ ጩኸቷንም ጸጥ ያደርጋል። ሞገዳቸው እንደ ታላቅ ውሃ ይተምማል፤ ጩኸታቸውም ያስተጋባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርሷም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፥ የድምፃቸውም ጩኸት ያስገመግማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ባሕር ሞገድ የሚያስገመግም ሠራዊት በድንገት በባቢሎን ላይ ደርሶ እየደነፋ አደጋ ይጥልባታል፤ በዚህም እኔ አጠፋታለሁ፤ ጸጥም አደርጋታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርስዋም ሞገዱ እንደ ብዙ ውኃዎች የሚተመውን ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ የድምፃቸው ጩኸት ተሰምቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርስዋም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፥ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፥ የድምፃቸውም ጩኸት ተሰምቶአል። |
ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤ የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤ በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች። የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣ በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።
ሰዎቹ እንደ ኀይለኛ ውሃ ጩኸት ቢያስገመግሙም፣ እርሱ ሲገሥጻቸው፣ በኰረብታ ላይ በነፋስ እንደሚበንን ትቢያ፣ በዐውሎ ነፋስ ፊት እንደሚበተን ገለባ ይበተናሉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ጢሮስ ሆይ፤ እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ባሕር ሞገዷን እንደምታስነሣ፣ ብዙ ሕዝብ አስነሣብሻለሁ።