ኤርምያስ 51:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እግዚአብሔር ቅንነታችንን መሰከረ፤ ኑ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ያደረገውን፣ በጽዮን እንናገር።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ጽድቃችንን በግልጥ አውጥቶአል፤ ኑ፥ በጽዮን የአምላካችንን የጌታን ሥራ እንናገር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን እንዲህ ተባባሉ፦ “እግዚአብሔር ለእኛ ትክክለኛ ፍርዱን ስለ ሰጠን ኑ! ወደ ኢየሩሳሌም ሄደን እግዚአብሔር አምላካችን ያደረገውን ሁሉ እንናገር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ፍርዳችንን አውጥቶአል፤ ኑ በጽዮን የአምላካችን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ጽድቃችንን አውጥቶአል፥ ኑ፥ በጽዮን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር። |
ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።
እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
እግዚአብሔር አምላካችን የተበቀለውን፣ ስለ ቤተ መቅደሱ የተበቀለውን በቀል፣ ከባቢሎን የመጡ ኰብላዮችና ስደተኞች፣ በጽዮን የሚናገሩትን ስሟቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደውን፣ በባቢሎናውያንም ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፤ ከመንጋው ታናናሹ ተጐትቶ ይወሰዳል፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።