ኤርምያስ 50:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባቢሎን ዘር የሚዘራውን፣ በመከር ጊዜ ማጭድ የጨበጠውንም ዐጫጅ አጥፉት፤ ከአጥፊው ሰይፍ የተነሣ፣ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለስ፤ ወደ ገዛ ምድሩም ይሽሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሪውንና መከር ሰብሳቢውን ከባቢሎን አስወግዱ፤ በዚያች አገር የሚኖር እያንዳንዱ የውጪ ዜጋ አደጋ የሚጥልባትን ሠራዊት በመፍራት ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ ከአረማዊው ሰይፍ ፊት የተነሣ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ ሀገሩ ይሸሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። |
ደጋግመው ይሰናከላሉ፣ አንዱም በሌላው ላይ ይወድቃል፤ ‘ተነሡ እንሂድ፤ ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ፤ ከጠላትም ሰይፍ እናምልጥ’ ይላሉ።
“ ‘ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እርሷ ግን ልትፈወስ አትችልም፤ ፍርዷ እስከ ሰማይ ስለ ደረሰ፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ስላለ፣ ትተናት ወደየአገራችን እንሂድ።’
ስለዚህ ጌታ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በየመንገዱ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ በአደባባዩም የሥቃይ ጩኸት ይሆናል፤ ገበሬዎች ለልቅሶ፣ አልቃሾችም ለዋይታ ይጠራሉ።