መወጠሪያ ገመድህ ላልቷል፤ ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ ሸራው አልተወጠረም፤ በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤ ዐንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል።
ኤርምያስ 50:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ምድር ትዘረፋለች፤ የሚዘርፏትም ሁሉ እስኪበቃቸው ይመዘብሯታል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች፥ የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎን ትመዘበራለች፤ በዝባዥዎችዋም እስከሚበቃቸው ድረስ ያገኙትን ሁሉ ይወስዳሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከላውዴዎን ምድር ትዘረፋለች፤ የማረኳትም ሁሉ ይጠግባሉ፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች፥ የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
መወጠሪያ ገመድህ ላልቷል፤ ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ ሸራው አልተወጠረም፤ በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤ ዐንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል።
በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ።
“ነገር ግን ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ሕዝቡን፣ የባቢሎናውያንንም ምድር ስለ በደላቸው እቀጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለዘላለምም ባድማ አደርጋታለሁ፤
የርሱ አገር በተራው ለሌሎች እስከሚገዛበት ጊዜ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ለርሱ፣ ለልጁና ለልጅ ልጁ ይገዛሉ፤ በዚያ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችና ታላላቅ ነገሥታት እርሱን ይገዙታል።
ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣ በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ! ለዝርፊያም ይሆናሉ።
የጽዮን ነዋሪዎች፣ እንዲህ ይላሉ፤ በሥጋችን ላይ የተፈጸመው ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን፤” ኢየሩሳሌም እንዲህ ትላለች፤ “ደማችን በባቢሎን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን።”
መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ በተሰጠው ራእይም በባቢሎን ምድር ወደ ነበሩት ምርኮኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ወጥቶ ሄደ፤
አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ፣ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን፣ በውስጣቸው የሚኖሩትን ሁሉ አጥፍተሃል።