ኤርምያስ 48:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፣ በሕዝብም አደባባዮች፣ ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤ እንደማይፈለግ እንስራ፣ ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብን ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ሰብሬዋለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብን እንደማይፈለግ ዕቃ ስለ ሰበርኳት በቤት ሰገነቶች ላይና በሕዝብ አደባባዮች ሁሉ ከለቅሶ በቀር ሌላ የሚሰማ ነገር የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞአብንም ለምንም እንደማይጠቅም ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞአብ ሰገነት ሁሉ ላይ፥ በአደባባዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብን እንደማይወደድ ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ከስብርባሪዎቹም መካከል፣ ለፍም መጫሪያ፣ ለውሃ መጥለቂያ ገል እስከማይገኝ ድረስ፣ ምንም ሳይቀር ክፉኛ እንደሚንኰታኰት፣ የሸክላ ዕቃ ይደቅቃል።”
እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ።
ይህ ኢኮንያን የተባለ ሰው፣ የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣ ማንም የማይፈልገው ዕቃ ነውን? እርሱና ልጆቹ ለምን ወደ ውጪ ተጣሉ? ወደማያውቁትስ ምድር ለምን ተወረወሩ?
እናንተ እረኞች፤ አልቅሱ፤ ዋይ በሉ፤ እናንተ የመንጋው ጌቶች፤ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ የምትታረዱበት ቀን ደርሷልና፤ እንደ ውብ የሸክላ ዕቃ ወድቃችሁ ትከሰከሳላችሁ።