ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍነው ድረስ፣ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷንም ቢሆን ባለወንጭፉ ሰራዊት ከብቦ አደጋ ጣለባት።
ኤርምያስ 48:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጕራል፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጕራል። ያከማቹት ንብረት ጠፍቷልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና፤ ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ድምፅ ይቃትታል፥ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ድምፅ ይቃትታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሞአብና በቂርሔሬስ የሚኖሩ ሕዝብ የነበራቸውን ሁሉ በማጣታቸው ምክንያት በዋሽንት ተመርተው እንደሚያለቅሱ ሰዎች አለቅስላቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና ስለዚህ ልቤ ለሞአብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል፤ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና፥ ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል፥ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል። |
ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍነው ድረስ፣ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷንም ቢሆን ባለወንጭፉ ሰራዊት ከብቦ አደጋ ጣለባት።
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።
ከተቀደሰው፣ ከተከበረውና ከፍ ካለው ዙፋንህ፣ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ኀይልህና ቅናትህ የት አለ? ገርነትህና ርኅራኄህ ከእኛ ርቀዋል።
ሀብትን በግፍ የሚያከማች ሰው፣ ያልፈለፈለችውን ጫጩት እንደምትታቀፍ ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ ትቶት ይሄዳል፤ በመጨረሻም ሞኝነቱ ይረጋገጣል።
ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ! ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤ አወይ፣ የልቤ ጭንቀት! ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ ዝም ማለት አልችልም፤ የመለከትን ድምፅ፣ የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና።