ኤርምያስ 43:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጣፍናስም የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
በግብጽ ሰሜናዊ ክፍል በሚግዶል፣ በጣፍናስና በሜምፊስ እንዲሁም በግብጽ ደቡባዊ ክፍል ስለሚኖሩት የአይሁድ ሕዝብ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤
“ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’
የግብጽን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል። በደመና ትሸፈናለች፤ መንደሮቿም ይማረካሉ።