ኤርምያስ 42:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ዛሬ በግልጽ ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ልኮኝ የነገርኋችሁን ሁሉ አሁንም አልታዘዛችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ዛሬ ነገርኋችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እናንተ በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የጌታን ድምፅ አልሰማችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ዛሬ እኔም መልሱን ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድነግራችሁ በእኔ አማካይነት ለላከላችሁ ቃል ሁሉ ታዛዦች አልሆናችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፥ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም። |
ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና፣ የጦር መኰንኖቹ ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ በሙሉ እግዚአብሔር በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን ቃል አልሰሙም።
ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት ሕዝቤ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህንም ለመስማት ከፊትህ ይቀመጣሉ፤ ነገር ግን አይፈጽሙትም። በከንፈራቸው ብዙ ፍቅርን ይገልጣሉ፤ ልባቸው ያረፈው ግን ተገቢ ባልሆነ ጥቅም ላይ ነው።
ቃልህን ሰምተው ሥራ ላይ የማያውሉት በመሆናቸው፣ አንተ ለእነርሱ በአማረ ድምፅ የፍቅር ዘፈን የሚዘፍን፣ በዜማ መሣሪያም አሳምሮ የሚጫወት ሙዚቀኛ ሆነህላቸዋል።
እንዲህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፣ በልቡ ራሱን በመባረክ፣ “እንደ ልቤ ሐሳብ ብኖርም እንኳ ሰላም አለኝ” ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።
ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤