እያንዳንዱም በፊቱ የገጠመውን ጠላት ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዷቸው ጀመር። የሶርያ ንጉሥ ቤን ሃዳድ ግን በፈረሱ ላይ ሆኖ ከጥቂት ፈረሰኞቹ ጋራ አመለጠ።
ኤርምያስ 41:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ዐብረውት ከነበሩት ስምንት ሰዎች ጋራ ከዮሐናን አመለጠ፤ ሸሽቶም ወደ አሞናውያን ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስማኤልና ስምንት ሰዎቹ ግን ከዮሐናን እጅ አምልጠው ወደ ዐሞን ምድር ኰበለሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ፥ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ። |
እያንዳንዱም በፊቱ የገጠመውን ጠላት ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዷቸው ጀመር። የሶርያ ንጉሥ ቤን ሃዳድ ግን በፈረሱ ላይ ሆኖ ከጥቂት ፈረሰኞቹ ጋራ አመለጠ።
ነገር ግን በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዝርያ የነበረው የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ዐሥር ሰዎች ይዞ መጥቶ ጎዶልያስንና በምጽጳ ዐብረውት የነበሩትን የይሁዳን ሰዎችና ባቢሎናውያንን ገደለ።
የናታንያ ልጅ እስማኤልና ዐብረውት የነበሩ ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው፣ የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ የሾመውን የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱት፤ ገደሉትም።
የደሴቲቱ ነዋሪዎች እባብ በእጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነፍስ ገዳይ ነው፤ ከባሕር ቢያመልጥ እንኳ የፍርድ አምላክ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።
ዳዊት፣ ከዚያች ዕለት ማታ ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ ወጋቸው፤ በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በቀር፣ ከመካከላቸው ያመለጠ አንድም አልነበረም።