ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ።”
ኤርምያስ 39:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን ግን በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ለምትፈራቸው ሰዎች ዐልፈህ አትሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምትፈራቸውም ሰዎች እጅ ተላልፈህ አትሰጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በዚያን ቀን እኔ እግዚአብሔር አንተን አድንሃለሁ፤ ለምትፈራቸው ጠላቶችህ ተላልፈህ አትሰጥም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊታቸውም የተነሣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። |
ከዚህም በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ።”
ኤርምያስ ለሕዝቡ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ሰፋጥያስ፣ የጳስኮር ልጅ ጎዶልያስ፣ የሰሌምያ ልጅ ዮካል እንዲሁም የመልክያ ልጅ ጳስኮር ሰሙ፤ ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፦
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ በኤርምያስ ላይ ባደረጉት ነገር ሁሉ ክፋትን አድርገዋል፤ ከከተማዪቱም እንጀራ በጠፋ ጊዜ በራብ እንዲሞት ጕድጓድ ውስጥ ጥለውታል።”
ስለዚህ ንጉሡ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ዳንኤልን አመጡት፤ ወደ አንበሶችም ጕድጓድ ጣሉት። ንጉሡም ዳንኤልን፣ “ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ያድንህ!” አለው።