ኤርምያስ 39:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቡሸዝባን፣ ከፍተኛ ሹሙ ኤርጌል ሳራስር እንዲሁም ሌሎች የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን፥ የራፋስቂሱ ናቡሽዝባንም የራብማጉ ኤርጌል ሳራስርም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ናቡዛርዳን፥ ናቡሻዝባንና ኔርጋልሻሬጼር ተብለው ከሚጠሩትና ከሌሎችም የባቢሎን ባለ ሥልጣኖች ጋር ሆኖ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዞች አለቃ ናቡዛርዳንም ላከ፤ ናቡሻዝባንም፥ ራፋስቂስም፥ ኔርጋል ሴራአጼርም፥ ራብማግም፥ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ላከ፥ ናቡሽዝባንም ራፋስቂስም ኤርጌል ሳራስርም ራብማግም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ ላኩ፥ |
ልከው ኤርምያስን ከዘበኞች አደባባይ አስወጡት፤ የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ ቤቱ እንዲወስደው በዐደራ ሰጡት፤ ኤርምያስም በራሱ ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፦ የሳምጋሩ ኤርጌል ሳራስር፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቦሠርሰኪም፣ ከፍተኛው ሹም ኤርጌል ሳራሳር እንዲሁም ሌሎቹ የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር ተቀመጡ።