ኤርምያስ 39:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንብረት ያልነበራቸውን ድኾች ግን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በይሁዳ ምድር ተዋቸው፤ በዚያ ጊዜም የወይን አትክልት ቦታና የዕርሻ መሬት ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ምንም የሌላቸውን አንዳንድ ድሆች በይሁዳ አገር ተዋቸው፥ በዚያው ጊዜም የወይኑን ቦታዎችና እርሻዎችን ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ሀብት ያልነበራቸውን ድኾች ብቻ በይሁዳ ምድር ተወ፤ ለእነርሱም የወይን ተክል ቦታዎችንና የሚያርሱት መሬት ሰጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ግን አንዳች ከሌላቸው ከሕዝቡ ድሆች ከፊሎቹን በይሁዳ ሀገር ተዋቸው፤ የወይኑን ቦታና እርሻውንም በዚያ ጊዜ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዳች ከሌላቸው ከሕዝቡ ድሆች ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በይሁዳ አገር ተዋቸው፥ የወይኑን ቦታና እርሻውን በዚያን ጊዜ ሰጣቸው። |
እኔም ራሴ ወደ እኛ በሚመጡት በባቢሎናውያን ፊት ልቆምላችሁ፣ በምጽጳ እቀመጣለሁ፤ እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬና ዘይት አምርቱ፤ በማከማቻ ዕቃዎቻችሁ ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞች ተቀመጡ።”
በየሜዳው የነበሩት የጦር መኰንኖችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ እንደ ሾመውና ወደ ባቢሎን በምርኮ ባልተወሰዱት በምድሪቱ ድኾች ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠው በሰሙ ጊዜ፣
በተጨማሪም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን እንዲሁም የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን በአኪቃም ልጅና በሳፋን የልጅ ልጅ በጎዶልያስ እጅ የተዋቸውን የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርያን ልጅ ባሮክን ወሰዷቸው፤
“የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር በፍርስራሾች ውስጥ የሚኖሩት ሕዝቦች፣ ‘አብርሃም አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ያም ሆኖ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛ ግን ብዙዎች ነን፤ በርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች’ ይላሉ።
ስለዚህ ለዕርድ የተለዩትን በጎች፣ በተለይም የተጨቈኑትን አሰማራሁ። ሁለት በትሮች ወስጄም፣ አንዱን “ሞገስ” ሌላውንም “አንድነት” ብዬ ጠራኋቸው፤ መንጋውንም አሰማራሁ።