የባቢሎንም ንጉሥ ከግብጽ ደረቅ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ የነበረውን ግዛቱን ሁሉ ወስዶበት ስለ ነበር፣ የግብጽ ንጉሥ ከአገሩ ዳግም ለዘመቻ አልወጣም።
ኤርምያስ 37:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈርዖንም ሰራዊት ከግብጽ ወጥቶ ነበርና ኢየሩሳሌምን ከብበው የነበሩት ባቢሎናውያን ይህን ሲሰሙ ኢየሩሳሌምን ለቅቀው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከበበ፤ ነገር ግን የግብጽ ሠራዊት ድንበሩን አልፎ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ወደ ኋላው አፈገፈገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንም ሠራዊት ከግብፅ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬአቸውን በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ። |
የባቢሎንም ንጉሥ ከግብጽ ደረቅ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ የነበረውን ግዛቱን ሁሉ ወስዶበት ስለ ነበር፣ የግብጽ ንጉሥ ከአገሩ ዳግም ለዘመቻ አልወጣም።
“ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ነፍሳቸውን ለሚሹ ጠላቶቻቸው ይኸውም ለጊዜው እናንተን ከመውጋት ለተመለሱ ለባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ትጠይቁኝ ዘንድ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ ‘ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሰራዊት ወደ ገዛ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል፤
ንጉሡ ግን በርሱ ላይ ዐመፀ፤ ፈረሶችና ብዙ ሰራዊት ለማግኘት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ይሳካለት ይሆን? እንዲህ ዐይነቱን ነገር የፈጸመ ያመልጣልን? ውል ያፈረሰስ ሳይቀጣ ይቀራልን?
በባቢሎናውያን ብዙ ሕይወት ለማጥፋት በከተማዪቱ ዙሪያ ዐፈር በሚደለድሉበትና ምሽግ በሚሠሩበት ጊዜ፣ ፈርዖን ከኀያል ሰራዊቱና ከብዙ ጭፍሮቹ ጋራ በጦርነት ሊረዳው አይችልም።