ስለዚህ፣ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላም ትቀበራለህ፤ በዚህ ቦታ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ” ሰዎቹም መልሷን ይዘው ወደ ንጉሡ ሄዱ።
ኤርምያስ 34:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰላም ትሞታለህ። ሕዝቡ ከአንተ በፊት ለነበሩት ነገሥታት አባቶችህ ክብር በቀብራቸው ጊዜ እሳት እንዳነደዱ፣ በቀብርህም ጊዜ ስለ ክብርህ እሳት ያነድዳሉ፤ “ዋይ ዋይ ጌታችን!” እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ ራሴ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰላም ትሞታለህ። ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት እንደ አባቶችህ ዕጣን እንደታጠነላቸው፥ እንዲሁ ለአንተም ዕጣንን ያጥኑልሃል፦ “ወየው! ጌታ ሆይ!” እያሉ ያለቅሱልሃል፤’ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰላም ታርፋለህ፤ ከአንተ በፊት ነገሥታት የነበሩ የቀድሞ አባቶችህ በሞቱ ጊዜ ሕዝቡ ለክብራቸው እሳት ያነዱላቸው እንደ ነበር ለአንተም እንዲሁ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ ንጉሣችን፥’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በሰላም ትሞታለህ፥ ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት አባቶችህ እሳት ይቃጠልላቸው እንደ ነበር እንዲሁ ያቃጥሉልሃልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለቅሱልሃል፤ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት እንደ አባቶችህ መቃጠል፥ እንዲሁ ያቃጥሉሃልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ እያሉ ያለቅሱልሃል፥ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ስለዚህ፣ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላም ትቀበራለህ፤ በዚህ ቦታ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ” ሰዎቹም መልሷን ይዘው ወደ ንጉሡ ሄዱ።
በዳዊት ከተማ ከዐለት አስፈልፍሎ ለራሱ ባሠራውም መቃብር ቀበሩት። በቅመማ ቅመምና በልዩ ልዩ ጣፋጭ ሽቱዎች በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፤ ስለ ክብሩም ትልቅ እሳት አነደዱ።
እነሆ፤ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላም ትቀበራለህ፤ በዚህ ቦታ እና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዐይኖችህ አያዩም።’ ” ሰዎቹም መልሷን ይዘው ወደ ንጉሡ ሄዱ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ “ ‘ዋይ ወንድሜ! ዋይ፣ እኅቴን!’ ብለው አያለቅሱለትም። ‘ዋይ፣ ጌታዬን! ዋይ፣ ለግርማዊነቱ!’ ብለውም አያለቅሱለትም።
“ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ መሐላውን ባቀለለበት፣ ውሉን ባፈረሰበት፣ በዙፋንም ላይ ባስቀመጠው ንጉሥ ምድር በባቢሎን ይሞታል።