ኤርምያስ 33:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔን ከበደሉበት ኀጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔ ላይ ያመፁበትንም ኀጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔም ላይ ከሠሩት ከበደላቸው ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔም ላይ ያመፁትንና የሠሩትን የበደላቸውን ኃጢአት ሁሉ ይቅር እላለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕጌን በመጣስ ከፈጸሙት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንና በዐመፅ የፈጸሙትን ሥራ ሁሉ ይቅር እላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔንም ከበደሉበት ኀጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ እኔም የበደሉኝንና ያመፁብኝን ኀጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ እኔንም የበደሉኝን ያመፁብኝንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ። |
በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል።
ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ። የሚቃጠል መሥዋዕታቸውንና ሌሎች መሥዋዕቶቻቸውን፣ በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤ ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
በእነዚያ ጊዜያት፣ በዚያ ዘመን፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አንዳችም አይገኝም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፤ ከቶም የለም፤ እንዲተርፉ ያደረግኋቸውን ቅሬታዎች እምራለሁና።
የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ቅጣትሽ ያበቃል፤ እርሱም የስደትሽን ዘመን አያራዝምም፤ ነገር ግን አንቺ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፤ ኀጢአትሽን ይቀጣል፤ ክፋትሽንም ይፋ ያወጣል።
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከኀጢአታችሁ ሁሉ በማነጻችሁ ቀን፣ ከተሞቻችሁ እንደ ገና መኖሪያ ይሆናሉ። የፈረሱትም እንደ ገና ይታደሳሉ።
እንዲሁም ታማኝ ምስክር፣ ከሙታን በኵርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፣