እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’
ኤርምያስ 32:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካምን ነገር ለእነርሱ ከማድረግ እንዳልቈጠብና ከእኔም ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በውስጣቸው ላኖር ከእነርሱ ጋራ የዘላለም ቃል ኪዳን እገባለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ ጋር የዘለዓለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መልካም ነገር ከማድረግም አላቋርጥም፤ በእውነት እንዲፈሩኝ አደርጋለሁ። ከዚያም በኋላ ፊታቸውን ከእኔ ወደ ሌላ አይመልሱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም እንዳልመለስ፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘላለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፥ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ። |
እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’
ጆሯችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።
እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ስለሚመለሱ፣ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ ፊታቸውንም ወደዚያ ያቀናሉ። መጥተውም ከቶ በማይረሳ፣ በዘላለም ቃል ኪዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋራ ይጣበቃሉ።
ከእነርሱም ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ቃል ኪዳኑም የዘላለም ይሆናል። አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ፤ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ።