ኤርምያስ 32:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተማዪቱ ለባቢሎናውያን ዐልፋ እየተሰጠች፣ ‘መሬቱን በብር ግዛ፤ ግዥውንም በምስክሮች ፊት ፈጽም’ ትለኛለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳ ከተማይቱ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ ብትሰጥም፤ አቤቱ ጌታ ሆይ! አንተ ግን፦ “እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ” አልኸኝ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ከተማይቱ በባቢሎናውያን ልትያዝ ተቃርባ ሳለ መሬቱን በምስክሮች ፊት እንድገዛ ያዘዝከኝ አንተ ነህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እርሻውን በብር ግዛ፤ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተምሁ፤ ምስክሮችንም አቆምሁ፤ ከተማዪቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፥ ከተማይቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች። |
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት፣ የዕርሻ ቦታና የወይን አትክልት ስፍራ እንደ ገና ይገዛሉ።’
“እነሆ፤ ከተማዪቱን ለመያዝ የዐፈር ድልድል በዙሪያዋ ተሠርቷል፤ ከሰይፍ፣ ከራብና ከቸነፈር የተነሣ ከተማዪቱን ለሚወጓት ለባቢሎናውያን ዐልፋ ልትሰጥ ነው፤ እንደምታየውም የተናገርኸው እየተፈጸመ ነው።
“እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ፣ የአጎቴ ልጅ አናምኤል ወደ ዘብ ጠባቂዎቹ አደባባይ መጥቶ፣ ‘የመቤዠቱን ርስት የማድረጉ መብት የአንተ ስለ ሆነ፣ በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን መሬቴን ለራስህ እንዲሆን ግዛው’ አለኝ።” ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ፤
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለወንድሞቻችሁና ለወገኖቻችሁ ነጻነት አላወጃችሁምና አልታዘዛችሁኝም። እንግዲህ እኔ ነጻነት ዐውጅላችኋለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘ይኸውም በሰይፍ፣ በቸነፈርና በራብ የምትወድቁበት ነጻነት ነው። ለምድር መንግሥታት ሁሉ መሠቀቂያ አደርጋችኋለሁ።