ኤርምያስ 30:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማዕበል፣ በቍጣ ይነሣል፤ የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣ በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የጌታ ዐውሎ ነፋስ! ቁጣው ወጥቶአል፥ ጥቅል ዐውሎ ነፍስ፤ እርሱም በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለው የእግዚአብሔር ቊጣ እንደ ኀይለኛ ነፋስ እየተገለባበጠ በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ የእግዚአብሔር ቍጣ ለመቅሠፍት ወጥቶአል፤ የመዓቱንም ጥፋት በኃጥኣን ራስ ላይ አምጥቶአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል፥ የዓመፀኞችንም ራስ ይገለባብጣል። |
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋት፣ ከአገር ወደ አገር እየተዛመተ መጥቷል፤ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ፣ ከምድር ዳርቻ ተነሥቷል።”
በዚያ ጊዜ፣ ለእዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን፣ ከዚያ የበረታ የሚጠብስ ደረቅ ነፋስ በምድረ በዳ ካሉት ባድማ ኰረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ
“እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን?
እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ይገለጣል፤ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፤ ጌታ እግዚአብሔር መለከት ይነፋል፤ በደቡብም ዐውሎ ንፋስ ውስጥ ይጓዛል፤