ናቡከደነፆር ዮአኪንን ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እንዲሁም የንጉሡን እናት፣ ሚስቶቹን፣ ሹማምቱና በአገር የታወቁትን ታላላቅ ሰዎችም ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ወሰደ።
ኤርምያስ 22:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት ወደ ሌላ አገር ወርውሬ እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተንም፥ የወለደችህ እናትህንም እንድትሰደዱ አደርጋለሁ፤ ማንኛችሁም ወዳልተወለዳችሁበት አገር ሄዳችሁ ሁላችሁም እዚያ ትሞታላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተንም፥ የወለደችህን እናትህንም ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ ሀገር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ። |
ናቡከደነፆር ዮአኪንን ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እንዲሁም የንጉሡን እናት፣ ሚስቶቹን፣ ሹማምቱና በአገር የታወቁትን ታላላቅ ሰዎችም ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ወሰደ።
ዮአኪን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። እናቱ ኔስታ ትባላለች፤ እርሷም የኢየሩሳሌም ሰው የኤልናታን ልጅ ነበረች።
የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን ዮርማሮዴክ በባቢሎን በነገሠ በዓመቱ ዮአኪንን ከወህኒ ፈታው።
ስለዚህ ከዚህች ምድር አውጥቼ፣ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤ ምሕረትንም አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።’
የይሁዳንም ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ ሌሎች ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱትንም ሁሉ ወደዚህ ስፍራ እመልሳለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ የጫነባቸውን ቀንበር እሰብራለሁና።’ ”
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እቴጌዪቱ እናቱ፣ የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መሪዎች፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ብረት ቀጥቃጮች ተማርከው ከኢየሩሳሌም ከተወሰዱ በኋላ ነበር።
ወደ ግብጽ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ”