ኤርምያስ 22:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዝግባ ዕንጨት ብዛት፣ የነገሥህ ይመስልሃልን? አባትህስ ፍትሕንና ጽድቅን በማድረጉ፣ የሚበላውና የሚጠጣው ጐድሎት ነበርን? እነሆ፤ ሁሉም መልካም ሆነለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ ይበላና ይጠጣ ፍርድንና ጽድቅን ያደርግ አልነበረምን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ሰዎች ከሚያደርጉት ይበልጥ ምርጥ በሆነ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቤትህን በመሥራትህ የተሻልክ ንጉሥ የሆንክ ይመስልሃልን? አባትህ ደስታ የሞላበት ሙሉ ዕድሜ ነበረው፤ እርሱ ዘወትር ትክክለኛና ቅን ከመሆኑ የተነሣ የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባትህ ዝግባ አዳራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። |
በአንተ ደስ ተሰኝቶ በእስራኤል ዙፋን ላይ ያስቀመጠህ እግዚአብሔር አምላክህ ቡሩክ ይሁን፤ እግዚአብሔር በዘላለም ፍቅሩም እስራኤልን ከመውደዱ የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን አንተን ንጉሥ አደረገህ።”
በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ፣ በፍጹም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ፣ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ፣ ከርሱ በፊትም ሆነ ከርሱ በኋላ ፈጽሞ አልተነሣም።
ኢዮስያስ ግን ሌላ ሰው መስሎ በጦርነት ሊገጥመው ወጣ እንጂ ወደ ኋላ አልተመለሰም፤ በመጊዶ ሜዳ ላይ ሊዋጋው ሄደ እንጂ፣ ኒካዑ ከእግዚአብሔር ታዝዞ የነገረውን ሊሰማ አልፈለገም።
ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።
የዳዊት ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ካደረጋችሁት ክፋት የተነሣ፣ ቍጣዬ እንዳይቀጣጠል፣ ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል እንዳይነድድ፣ በየማለዳው ፍትሕን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ሰው፣ ከጨቋኙ እጅ አድኑት።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ “ ‘ዋይ ወንድሜ! ዋይ፣ እኅቴን!’ ብለው አያለቅሱለትም። ‘ዋይ፣ ጌታዬን! ዋይ፣ ለግርማዊነቱ!’ ብለውም አያለቅሱለትም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።
“እነሆ፤ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቅርንጫፍ የማስነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ እርሱም ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ፣ በጥበብ የሚገዛ ንጉሥ ይሆናል” ይላል እግዚአብሔር።
አምላካችንን እግዚአብሔርን በመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንታዘዛለን።”
ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለዘላለም በሚሰጥህም ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ጠብቅ።