ኤርምያስ 20:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፣ ማሕፀንም ሰፊ የዘላለም ማደሪያዬ እንዲሆን፣ ከማሕፀንም ሳልወጣ አልገደለኝምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናቴ መቃብር እንድትሆነኝ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ እንዲቆይ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብር እንድትሆነኝ ምነው በእናቴ ማሕፀን በገደለኝ ኖሮ! የእናቴ ማሕፀንም ለሁልጊዜ ትልቅ ሆኖ በኖረ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፥ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቈይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቆይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና። |
አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሠኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤
ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል።