ኤርምያስ 20:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤ የድኻውን ነፍስ፣ ከክፉዎች እጅ ታድጓልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ዘምሩ ጌታንም አመስግኑ፤ የችግርተኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ዘምሩ! ጌታን አመስግኑ! እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ አመስግኑትም፤ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፥ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና። |
ለድኻ መጠጊያ፣ በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣ ከማዕበል መሸሸጊያ፣ ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል። የጨካኞች እስትንፋስ፣ ከግድግዳ ጋራ እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ፤ ስለ ሕዝቦች አለቃ እልል በሉ፤ ምስጋናችሁን አሰሙ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ የእስራኤልን ቅሬታ፣ ሕዝብህን አድን’ በሉ።