ኤርምያስ 18:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤ በመጥፊያቸው ቀን፣ ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠላት ፊት እንደ ምሥራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትቢያ በምሥራቅ ነፋስ እንደሚበተን፥ ሕዝቤን በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። ፊቴን ከእነርሱ መልሼ ጀርባዬን እሰጣቸዋለሁ። ጥፋት በሚመጣባቸውም ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠላት ፊት እንደ በረሃ ዐውሎ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፤ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠላት ፊት እንደ ምሥራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም። |
ዛፉን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ’ ድንጋዩንም፣ ‘አንተ ወለድኸኝ’ አሉ፤ ፊታቸውን ሳይሆን፣ ጀርባቸውን ሰጥተውኛልና፤ በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ‘መጥተህ አድነን’ ይላሉ።
ቅጥረኞች ወታደሮቿም እንደ ሠቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣ እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፤ በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።
በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣ የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ ምንጩ ይነጥፋል፤ የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል። የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።
እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀቂያ ትሆናለህ።
ከዚያም እግዚአብሔር ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትንሃል። በዚያ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከዕንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።
በዚያች ቀን እቈጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፣ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፣ አምላካችን ከእኛ ጋራ ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።
በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧል፤ የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።”