ኤርምያስ 16:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእነርሱ ጋራ ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣት ድግስ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመብላትና ለመጠጣት፥ ከእነርሱም ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰዎች ወደሚደሰቱበት ግብዣ ቤትም አትግባ፤ ለመብላትና ለመጠጣትም ከእነርሱ ጋር አትቀመጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትበላና ትጠጣ ዘንድ ከእነርሱ ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትበላና ትጠጣ ዘንድ ከእነርሱ ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ። |
ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከእነርሱም ጋራ አልፈነጨሁም፤ እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።
ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋራ እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋራ ምግብ እንኳ አትብሉ።