ኤርምያስ 15:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከእነርሱም ጋራ አልፈነጨሁም፤ እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ ለብቻዬ ተቀመጥሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥኩም አልተደሰትኩምም፤ ቁጣን ሞልተህብኛልና እጅህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ለብቻዬ ተቀመጥሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሚፈነጥዙ ሰዎች ጋር አልተወዳጀሁም፤ ከእነርሱም ጋር አልተደሰትኩም፤ ቊጣህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ብቻዬን ተቀመጥኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፤ ነገር ግን በእጅህ ፊት ፈርቻለሁ፤ ምሬትን ሞልተህብኛልና ለብቻዬ ተቀመጥሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፥ ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ። |
ባትሰሙ ግን፣ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣ ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤ እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።
በእነርሱ ላይ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፤ በውስጤም ልይዘው አልቻልሁም። “መንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናት፣ በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው፤ ባልም ሚስትም፣ ያረጁና የጃጁም አያመልጡም።
ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ፣ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በእነዚህ ሰባ ዓመታት ውስጥ የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።