ኢሳይያስ 7:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘ይህ ምክራቸው አይፈጸምም፤ ከቶም አይደረግም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልዑል እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦ ‘ይህ ምክራቸው አይፈጸምም፤ ከቶም አይደረግም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህ ምክራቸው አይጸናም፤ ከቶ ሊሆን አይችልም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም። |
ከሞት ጋራ የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤ ከሲኦልም ጋራ ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤ ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ እናንተም ትጠራረጋላችሁ።
በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፣ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’
የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም።
የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣ እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤ በሰማይ ኀይላት፣ በምድርም ሕዝቦች ላይ፣ የወደደውን ያደርጋል፤ እጁን መከልከል የሚችል የለም፤ “ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።