ኢሳይያስ 57:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይራ ዘይት ይዘሽ፣ ሽቱ በላዩ ጨምረሽ ወደ ሞሎክ ሄድሽ፤ መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ አገር ላክሽ፤ እስከ ራሱ እስከ ሲኦልም ዘለቅሽ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፥ ሽቱሽንም አበዛሽ፥ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፥ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ዘይትና ሽቶ ተቀብታችሁ ሞሌክ ወደ ተባለው ጣዖት ሄዳችሁ፤ የምታመልኳቸውን ጣዖቶች ለመፈለግ መልእክተኞቻችሁን ወደ ሩቅ ቦታ ወደ ሙታን ዓለም እንኳ ሳይቀር ላካችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝሙትሽን ከእነርሱ ጋር አበዛሽ፤ ከአንቺ የራቁ ብዙዎችንም ተጐዳኘሽ። መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፤ ከእነርሱም ጋር ተወገድሽ፤ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፥ ሽቱሽንም አበዛሽ፥ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፥ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ። |
ማንኛዋም አመንዝራ ሴት ዋጋ ይከፈላታል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ስጦታ ታበረክቻለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋራ ያመነዝሩ ዘንድ እጅ መንሻ ታቀርቢላቸዋለሽ።
“ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው።
“ንጉሡ ደስ እንዳለው ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን እጅግ ከፍ በማድረግ በአማልክት አምላክ ላይ ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የቍጣውም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ይሳካለታል፤ የተወሰነው ነገር ሁሉ መሆን አለበትና።
ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል።
ዐጕል ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ የሚወድድ ማንም ሰው እንዳያደናቅፋችሁ ተጠንቀቁ። እንደዚህ ያለ ሰው ስላየው ራእይ ከመጠን በላይ ራሱን እየካበ በሥጋዊ አእምሮው ከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይታበያል፤