ኢሳይያስ 4:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፣ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ ውርደታችንን አስቀርልን!” ይሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው “በምግብም ሆነ በልብስ ራሳችንን ችለን እንተዳደራለን፤ ‘ባል የላቸውም’ ተብለን ከመሰደብ እንድንድን የአንተ ሚስቶች ተብለን እንድንጠራ ብቻ ፍቀድልን” ብለው ይለምኑታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እንጀራችንን እንበላለን፤ የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰደባችንንም አርቅልን” ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፦ የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፥ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል። |
በዚያ ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፣ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፣ ከእንግዲህ ወዲህ በመታቸው ላይ አይታመኑም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ፣ በእውነት ይታመናሉ።
“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።
የመበለቶቻቸውን ቍጥር፣ ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ፤ የጐበዛዝት እናቶች በሆኑትም ላይ፣ አጥፊውን በቀትር አመጣባቸዋለሁ። ሽብርንና ድንጋጤን፣ በድንገት አወርድባቸዋለሁ።