በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፤ አጋራውያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ጸሎታቸውን ሰማ።
ኢሳይያስ 26:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ በአንተ ላይ ታምናለችና በሰላም ትጠብቃታለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ የምትደገፍ ነፍስን ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። |
በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፤ አጋራውያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ጸሎታቸውን ሰማ።
ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ቍጥር ካላቸው ሠረገላዎቻቸውና ፈረሶቻቸው ጋራ ኀያል ሰራዊት አልነበሩምን? ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጠህ፤
ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብጽ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!
አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ? ለእኔ ታማኝ እንደ ሆነ ሰው የታወረ፣ እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው?
እናንተ የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪዎች ነን ብላችሁ ራሳችሁን የምትጠሩ፣ በእስራኤል አምላክ የምትታመኑ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው የሚለውን አድምጡ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በተወደደ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤ በድነት ቀን እረዳሃለሁ። ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣ እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍች ወረቀት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰላምን እንደ ወንዝ ውሃ አፈስስላታለሁ፤ የመንግሥታትንም ብልጽግና እንደ ጅረት ውሃ አጐርፍላታለሁ፤ ትጠባላችሁ፤ በዕቅፏም ትያዛላችሁ፤ በጭኖቿም ላይ ትፈነድቃላችሁ።
ከዚያም ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፤ “መልአኩን ልኮ አገልጋዮቹን ያዳነ፣ የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ ይባረክ፤ በርሱ በመታመን የንጉሡን ትእዛዝ ጥሰው፣ ከአምላካቸው በቀር ሌላ አምላክ ለማገልገልም ሆነ ለርሱ ለመስገድ ፈቃደኛ ባለመሆን ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋልና።
ንጉሡ እጅግ ተደስቶ፤ ዳንኤልን ከጕድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጕድጓድ በወጣ ጊዜ፣ አንዳች ጕዳት አልተገኘበትም።
እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራዊ ምድራችንን ሲወርር፣ ምሽጎቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ ሰባት እረኞችን፣ እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።