ኢሳይያስ 2:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ዝቅ ብሏል፤ የሰው ልጅም ተዋርዷል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ዝቅ ብሏል፤ የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ በሁሉም ላይ ኀፍረትና ውርደት ይደርስባቸዋል፤ ጌታ ሆይ! በደላቸውን ይቅር አትበል! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፤ ታላቁም ሰው ተዋርዶአል፤ ኀጢአታቸውንም ይቅር አልላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፥ ጨዋውም ተዋርዶአል፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አትበላቸው። |
አንተ እግዚአብሔር አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤ በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ
አንተ ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ ሊገድሉኝ ያሤሩብኝን ሤራ ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህ ወድቀው የተጣሉ ይሁኑ፤ በቍጣህም ጊዜ አትማራቸው።
ዐጕል ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ የሚወድድ ማንም ሰው እንዳያደናቅፋችሁ ተጠንቀቁ። እንደዚህ ያለ ሰው ስላየው ራእይ ከመጠን በላይ ራሱን እየካበ በሥጋዊ አእምሮው ከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይታበያል፤
እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም።
ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ እርሱ ቅዱስ አምላክና፤ ቀናተኛም አምላክ ነው፤ ዐመፃችሁን ወይም ኀጢአታችሁን ይቅር አይልም።