ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋራ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ምርጥ ዱቄትን ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋራ ለውስና ሩብ ሂን ወይንን ደግሞ የመጠጥ መሥዋዕት በማድረግ አቅርብ።
ሆሴዕ 9:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈስሱም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሠኘውም፤ እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ። ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም የወይን ጠጅን ቁርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘን እንጀራም ይሆንባቸዋል፥ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ፤ እንጀራቸውም ለሆዳቸው ይሆናል እንጂ ወደ ጌታ ቤት አይገባም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ መባ ማቅረብ አይችሉም፤ መሥዋዕታቸውም እግዚአብሔርን አያስደስትም፤ የእነርሱ እንጀራ ሲርባቸው የሚበሉት እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ አይደለም፤ ስለዚህ ለእነርሱ የእዝን እንጀራ ይሆናል፤ እርሱንም የሚመገብ ሁሉ ይረክሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቍርባን አያቀርቡም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘንም እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፤ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቍርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፥ የኀዘንም እንጀራ ይሆንላቸዋል፥ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፥ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም። |
ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋራ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ምርጥ ዱቄትን ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋራ ለውስና ሩብ ሂን ወይንን ደግሞ የመጠጥ መሥዋዕት በማድረግ አቅርብ።
በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮች ውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን?
ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።
ዕጣን ከሳባ ምድር፣ ጣፋጩ ከሙን ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመኛል? የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን አልቀበልም፤ ሌላውም መሥዋዕታችሁ ደስ አያሰኙኝም።”
ድምፅህን ዝቅ አድርገህ በሐዘን አንጐራጕር እንጂ ለሞተው አታልቅስ። ጥምጥምህን ከራስህ አታውርድ፤ ጫማህንም አታውልቅ፤ አፍህ ድረስ አትሸፋፈን፤ የዕዝን እንጀራም አትብላ።”
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው፤ መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በዚህም ምክንያት በግብጽ ምድር፣ መዘባበቻ ይሆናሉ።”
ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።
በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው።
ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ።
ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።
የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልቀበለውም፤ ከሠቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልመለከተውም።
ሌላው የምታደርጉት ነገር ደግሞ፣ የእግዚአብሔርን መሠዊያ በእንባ ታጥለቀልቃላችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቍርባናችሁን ስለማይመለከትና በደስታም ከእጃችሁ ስለማይቀበል ታለቅሳላችሁ፤ ትጮኻላችሁም።
“ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ስጣቸው፤ ‘ሽታው ደስ እንዲያሠኘኝ በእሳት የሚቀርብልኝን የምግብ ቍርባን የተወሰነውን ጊዜ ጠብቃችሁ አቅርቡልኝ።’
“በገጸ ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ይዘርጉበት፤ በላዩም ላይ ወጭቶች፣ ጭልፋዎች፣ ጽዋዎች፣ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች እንዲሁም ሁልጊዜ ከዚያ የማይታጣውን ኅብስት ያስቀምጡ።
ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው።”
በሐዘን ላይ ሳለሁ፣ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚሁ ላይ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም፤ አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።