ሆሴዕ 8:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን!’ እያሉ፣ ወደ እኔ ይጮኻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “አምላክ ሆይ! እኛ እስራኤል እናውቅሃለን!” ብለው ወደ እኔ ጮሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም፥ “አምላክ ሆይ! እኛ ሕዝብህ እናውቅሃለን” እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክ ሆይ! እኛ እስራኤል ዐወቅንህ ብለው ወደ እኔ ይጮኻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አምላክ ሆይ፥ እኛ እስራኤል አወቅንህ ብለው ወደ እኔ ይጮኻሉ። |
መሪዎቿ በጕቦ ይፈርዳሉ፤ ካህናቷ ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ ነቢያቷም ለገንዘብ ይጠነቍላሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈውም፣ “እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይደርስብንም” ይላሉ።
የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደ ሆናችሁና ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል።