ሆሴዕ 7:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እርሱንም አልፈለገም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ትዕቢት በራሱ ላይ መስክሮአል፤ ወደ አምላካቸው ወደ ጌታ ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ትምክሕታቸው በራሳቸው ላይ ይመሰክርባቸዋል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ ወደ አምላካቸው አልተመለሱም ከቶም አልፈለጉኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ውርደቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፤ በዚህም ሁሉ እግዚአብሔርን አልፈለጉትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ መሰከረ፥ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም። |
ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
“ከመቃብር ኀይል እታደጋቸዋለሁ፤ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ፤ መቅሠፍትህ የት አለ? መቃብር ሆይ፤ ማጥፋትህ የት አለ? “ከእንግዲህ ወዲህ አልራራለትም፤
የቀደሙት ነቢያት፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ይላል በማለት ለአባቶቻችሁ ሰብከው ነበር፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤” ይላል እግዚአብሔር።