ሆሴዕ 5:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቅጣት ቀን፣ ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣ በእስራኤል ነገዶች መካከል፣ በርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም በተግሣጽ ቀን ባድማ ይሆናል፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል እርግጥ የሆነውን ነገር አሳውቂያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅጣት ቀን እስራኤል ባድማ ትሆናለች፤ ይህም በእርግጥ እኔ በእስራኤል ነገዶች ላይ እንዲደርስ የወሰንኩት ጥፋት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬም በዘለፋ ቀን ለጥፋት ይሆናል፤ በእስራኤልም ነገዶች የታመነውን ነገር አሳየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም በዘለፋ ቀን የፈረሰ ይሆናል፥ በእስራኤል ነገዶች ዘንድ በእርግጥ የሚሆነውን ነገር ገልጫለሁ። |
እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።
ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ገና ድሮ ነገርሁህ፤ ከመፈጸማቸው በፊት አስታወቅሁህ፤ ይህም፣ ‘ጣዖቶቼ ይህን አደረጉ፤ ከዕንጨት የተቀረጸው ምስልና ከብረት የተሠራው አምላኬ ይህን ወስኗል’ እንዳትል ነው።
እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።
የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ ተማርኮ ይሄዳል።’ ”
ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”