ሆሴዕ 2:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ እተክላታለሁ፤ ‘ምሕረትን ያላገኘ’ ብዬ የጠራሁትንም እምረዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብለው የተጠሩትንም፣ ‘ሕዝቤ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም፣ ‘አንተ አምላኬ ነህ’ ይላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዲህም ይሆናል፥ በዚያን ቀን እመልሳለሁ ይላል ጌታ፥ ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤን በምድሪቱ ላይ እመሠርታለሁ፤ እንዲበለጽጉም አደርጋቸዋለሁ፤ ‘ምሕረት አይደረግላችሁም’ የተባሉትን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ የተባሉትንም ‘ሕዝቤ ናችሁ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘አንተ አምላካችን ነህ’ ይሉኛል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ላይ ለእኔ እዘራታለሁ፤ ይቅርታ የሌላትን ይቅር እላታለሁ፤ ያልተወደደች የነበረችውን እወድዳታለሁ፤ ሕዝቤም ያልሆነውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለዋለሁ፤ እርሱም፥ “አንተ ጌታዬና አምላኬ ነህ” ይለኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያንም ቀን እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል፥ |
በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።
አንዱ፣ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው ራሱን በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ በእጁ ላይ ‘የእግዚአብሔር ነኝ’ ብሎ ይጽፋል፤ ራሱን በእስራኤል ስም ይጠራል።
ብርታቴና ምሽጌ፣ በመከራ ቀን መጠጊያዬ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አሕዛብ ከምድር ዳርቻ፣ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “አባቶቻችን ለአንዳች ነገር ያልረቧቸውን ከንቱ ጣዖቶች፣ የሐሰት አማልክትን ወረሱ።
የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ከልጆቹም በአብርሃም፣ በይሥሐቅና በያዕቆብ ዘር ላይ ገዥ እንዲሆኑ አልመርጥም፤ ይህንም የምለው ምርኳቸውን ስለምመልስና ስለምራራላቸው ነው።’ ”
ጎሜር እንደ ገና ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “ይቅር እላቸው ዘንድ ለእስራኤል ቤት ከእንግዲህ ስለማልራራላቸው፣ ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት።
ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”
ከዚያም ኢየሩሳሌምን ከወጓት አሕዛብ ከሞት የተረፉት ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ።
“በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።
“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።