ሆሴዕ 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን “ባለቤቴ” ብላ እንጂ እንደ በዓል ጣዖት “ጌታዬ” ብላ አትጠራኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ በዓሊም ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ። |
ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።
“ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ።
ውሽሞቿን ተከትላ ትሄዳለች፤ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም። ከዚያም እንዲህ ትላለች፤ ‘ወደ ቀድሞ ባሌ እመለሳለሁ፤ የፊተኛው ኑሮዬ ከአሁኑ ይሻለኛልና።’
ሙሽራዪቱ የሙሽራው ናት፤ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን፣ የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል።
ባሏ ታርቆ ሊመልሳት ወደ እርሷ ሄደ፤ ሲሄድም አሽከሩንና ሁለት አህዮችን ይዞ ነበር፤ ሴቲቱም ወደ አባቷ ቤት አስገባችው፤ አባቷም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀበለው።
እርሷም መልሳ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ምንም እንኳ፣ ከሴት ሠራተኞችህ እንደ አንዲቱ መቈጠር የማይገባኝ ብሆንም፣ እንድጽናና አድርገኸኛል፤ እንዲሁም እኔን አገልጋይህን በመልካም ንግግር ደስ አሠኝተኸኛል፤ ስለዚህ ሞገስህ እንዳይለየኝ እለምንሃለሁ” አለችው።