ሆሴዕ 13:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬም ሲናገር ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤ በእስራኤልም የተከበረ ነበር፤ ነገር ግን በኣልን ስላመለከ በደለ፤ ሞተም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም መካከል ታበየ፤ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬም ነገድ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ከፍ ብሎ በነበረበት ዘመን ሲናገር የሚሰሙት ሁሉ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ በኋላ ግን ባዓል ለተባለ ጣዖት በመስገድ ኃጢአት ስለ ሠራ በሞት ተቀጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬም እንደ ተናገረ በእስራኤል ሥርዐቱን ወሰደ፤ ለበዓልም አደረገው፤ ሞተም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም ዘንድ ታበየ፥ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ። |
ከዚያም ኢዮርብዓም በኰረብታው አገር በኤፍሬም የምትገኘውን ሴኬምን ምሽግ አድርጎ ሠራ፤ በዚያም ተቀመጠ። ደግሞም ያን ትቶ በመውጣት የጵኒኤልን ምሽግ ሠራ።
እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጄ አልሠራችምን? እንዲገኙስ ያደረግሁ እኔ አይደለሁምን?” ይላል እግዚአብሔር። “ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።
እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣ እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።
ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ከሙሴ ጋራ እንደ ነበርሁ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ መሆኔን ያውቁ ዘንድ፣ በእስራኤል ሁሉ ፊት አንተን ከፍ ከፍ ማድረጌን በዛሬዋ ዕለት እጀምራለሁ።
የኤፍሬም ሰዎች ኀይላቸውን አሰባስበው ወደ ጻፎን በመሻገር ዮፍታሔን፣ “አሞናውያንን ለመውጋት ስትወጣ ዐብረንህ እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምንድን ነው? ቤትህን በላይህ ላይ እናቃጥለዋለን አሉት።”
በዚህ ጊዜ የኤፍሬም ሰዎች፣ “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ ለምን አልጠራኸንም? ለምንስ እንዲህ ያለ ነገር አደረግህ?” በማለት ጌዴዎንን እጅግ ነቀፉት።
ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “በዐይንህ ፊት ታናሽ የነበርህ ብትሆንም፣ የእስራኤል ነገዶች መሪ ሆነህ የለምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል።