የአሦር ንጉሥ ግን ሆሴዕ እንደ ከዳው ተገነዘበ፤ ምክንያቱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሲጎር መልክተኞች ስለ ላከና በየዓመቱም ያደርግ እንደ ነበረው ለአሦር ንጉሥ ስላልገበረ ነው፤ ከዚህም የተነሣ ስልምናሶር ይዞ ወህኒ ቤት አስገባው።
ሆሴዕ 12:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም ነፋስን ያሰማራል፥ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዓመጻን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬም ግን ክብርንና ከንቱ ነገርን የሚያሳድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦርም ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ ምሕረትም ያደርጉለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይትን ይልካል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፥ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፥ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ። |
የአሦር ንጉሥ ግን ሆሴዕ እንደ ከዳው ተገነዘበ፤ ምክንያቱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሲጎር መልክተኞች ስለ ላከና በየዓመቱም ያደርግ እንደ ነበረው ለአሦር ንጉሥ ስላልገበረ ነው፤ ከዚህም የተነሣ ስልምናሶር ይዞ ወህኒ ቤት አስገባው።
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣ በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰድደዋለሁ።
በኔጌብ ስላሉት እንስሳት የተነገረ ንግር፤ መልእክተኞች ሀብታቸውን በአህያ፣ ውድ ዕቃዎቻቸውን በግመል ጭነው፣ ተባዕትና እንስት አንበሶች፣ መርዘኛና ተወርዋሪ እባቦች በሚኖሩበት፣ መከራና ጭንቅ ባለበት ምድር ዐልፈው፣ ወደማይጠቅማቸው ወደዚያ ሕዝብ፣
እግዚአብሔር ከሕዝቦች ጋራ ይፋረዳልና፣ ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ያስተጋባል፤ በሰው ሁሉ ላይ ፍርድን ያመጣል፤ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ” ይላል እግዚአብሔር።
ለበኣል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው ቀናት እቀጣታለሁ፤ በጌጣጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች፤ ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች፤ እኔን ግን ረስታለች” ይላል እግዚአብሔር።
እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።
ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
“በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣ እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ ስለ ሠሩት ኀጢአት፣ ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም አልወድዳቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።
“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤ እናንተ የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋራ ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋራ ይፋረዳል።