ሆሴዕ 10:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤ በዚያም ጸናችሁ፤ በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ ጦርነት አልጨረሳቸውምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤል ሆይ! ከጊብዓ ዘመን ጀምረህ ኃጢአትን ሠርተሃል፤ በዚያ ጸንተዋል፤ በዓመፀኛ ልጆች ላይ በጊብዓ ጦርነት አይደርስባቸውምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በጊብዓ ኃጢአት ከሠሩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ከማሳዘን አልተቈጠቡም፤ ስለዚህ በገባዖን ጦርነት ይነሣባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኀጢአትን ሠርቶአል፤ በዚያም ጸንተዋል፤ በጊብዓ ላይ ጦር አይደርስባቸውምን? መጥቶም የዐመፅ ልጆችን ገሠጻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ሆይ፥ ከጊብዓ ዘመን ጀምረህ ኃጢአትን ሠርተሃል፥ በዚያ ጸንተዋል፥ በጊብዓ ላይ ሰልፍ አይደርስባቸውምን? |
እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።
የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣ የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤ እሾኽና አሜከላ ይበቅልባቸዋል፤ መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤ በዚያ ጊዜ ተራሮችን፣ “ውደቁብን!” ኰረብቶችንም፣ “ሸፍኑን!” ይላሉ።